አማርኛ
Article Index
ስለ ክልሉ አጠቃላይ እይታዎች
ቀጥሎ
All Pages
የመልካዓ ምድራዊ አቀማመጡን ስንመለከት ከባህር ወለል በላይ 500-2700 ሜትር የሚደርስ ከፍታ ያላቸው ቦታዎች ይገኛሉ፡፡ ከዓመት ዓመት የሚፈሱ እንደ ዳቡስ፣ ዴዴሳ፣ ካማሽ፣ ቱመት ሙካር፣ በለስና ዱራን የመሳሰሉ ትላልቅ የሚታወቁ ወንዞችና እንደ ጉብላክ፣ሸርቆሌ፣ሆሃና … ወዘተ ያሉ ጅረቶች የሚገኙበት መሆኑ ካልተነካው ድንግልና ለም መሬት ጋር ተዳምሮ ለኑሮና ለተለያዩ አትክልቶችና ፍራፍሬ፣የቅባትና የአገዳ እህሎች ተስማሚ አድርጎታል፡፡በዚህም መሰረት ክልሉ ለኑሮ ለተለያዩ የሰብል አይነቶች ተሥማሚ በመሆንና በማንጎና በቅርቀሀ ተክል ከሌሎች ክልሎች በተለየ ሁኔታ በአምራችነት ይታወቃል፡፡ እንደወርቅ፣እምነብረድ፣ሙጫና እጣን የመሳሰሉት እምቅ የተፈጥሮ ሃብቶች ያሉትና በመሰረተ ልማቱም በኩል በግብርናው ክፍለ-ኢኮኖሚ በሰብል ልማት፣በእንስሳት እርባታ፣በተፈጥሮ ሀብት ልማት፣በመስኖ እርሻ ልማትና የኢንቨስትመንት ምርትን ከማሳደግ አንጻር ምቹ መሆኑ፣በመሰረተ ልማት ግንባታ በትምህርትበጤናው ዘርፍ፣የመንገድ፣የንጹህ መጠጥ ውሃ፣የመብራትና የቴሌኮም፣የፖስታና የኢንሹራንስ እንዲሁም የባንክ አገልግሎቶች የተሟሉበት በመሆኑ ለኑሮና ለተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች ምቹ በመሆኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ ባለሀብቶች ቁጥር እየጨመረ የመጣበት ክልል ነው፡፡ከዚህም በተጨማሪ የዘመናዊ ስቴዲየምና የሃገሪቱን ቀልብ የሳበው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ መገኛ በመሆኑ በቀጣይ በቱሪስት ዘርፍ፣በአሳ እርባታና በተለያዩ የግብርና የእርሻራዎች ዘርፍ ተመራጭነቱ ስለሚጎላ የክልሉን ክፍለ-ኢኮኖሚ ከፍ እንደ ሚያደርገው ይጠበቃል፡፡

በክልሉ 5 ነባር ብሄረሰቦች የሚገኙ ሲሆን እነሱም በርታ፣ጉሙዝ፣ሽናሻ፣ማኦና ኮሞ ሲሆኑ ከሌሎች ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ጋር በመቻቻልና በመፈቃቀር በጋራ የሚኖሩበት ክልል ነው፡፡ ቀደም ሲል እንደ ሀገር ሲደርስ የነበረው ብሄራዊ ጭቆና የደረሰባቸው እንደመሆኑ መጠን የጥቂቶቹን የፊውዳል አገዛዝ አሜን ብለው ሳይቀበሉ ባገኙት አጋጣሚና ጊዜ ሁሉ በመታገል ለፊውዳላዊ ሥርዓት መገርሰስ የበኩላቸውን ድርሻ ያበረከቱ ሲሆን በዘውዳዊው አገዛዝ እግር ሥር ወድቆ የተተካው አምባገነኑ የደርግ መንግስትን ለመጣል በተካሄደው እልህ አስጨራሽ ትግል ከሌሎች የሃገራችን ብሄር፣ብሄረሰቦችና ህዝቦች ጋር በመሆን በከፈሉት መሰዋትነት ዘመን ተሻጋሪ ድል ለማስመዝገብ በቅተዋል፡፡ በዚህም በተለይ ራስን በራስ የመምራትና የማስተዳደር ጥያቄዎችን አዎንታዊ ምላሽ እንዲያገኙ ከማድረግም ባለፈ የዘመናት ጥያቄ የነበረውን በቋንቋቸው የመናገር፣በታሪካቸውና በባህላቸው የመታወቅና የመጠቀምን መብት ተጎናፅፈዋል፡፡ ብዝሃነትንም ለማስተናገድ የሚያስችል ፌድራላዊ የመንግስት ሥርዓት በማዋቀርና በመግባባት፣ በመከባበር፣በመቻቻልና፣በመፈቃቀድ መርህ ላይ የተመሰረተ ዴሞክራሲያዊ አንድነትን ለመፍጠር ችለዋል፡፡በሀገራችን የጋራ ጉዳይ ላይ በጋራ ለመምከርና ለመወሰን በሚያስችሏቸው የፌዴራል መዋቅሮች ውስጥ በፍትሃዊነት ለመሳተፍ በቅተዋል፡፡ በዚህም መሰረት የክልሉን ፖለቲካ፣ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ አጠናክሮ በማስቀጠል ክልሉ አሁን ለደረሰበት ደረጃ መነሻ ሆኖ ቀጥለዋል፡፡

  
ከተለያዩ የመንግስት አካላት ጋር በምን መልኩ መገናኘት ይመርጣሉ?