አማርኛ
Article Index
ስለ ክልሉ አጠቃላይ እይታዎች
ቀጥሎ
All Pages

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በኢትዮጵያ ከሚገኙት 9ኙ ክልሎች መካከል አንዷ ሲትሆን ከአዲስ አበባ በስተ ምዕራብ አቅጣጫ ላይ በ 672 .ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡ዋና ከተማዋም አሶሳ የተቆረቆረችሁ በ1886 ዓ/ም እንደሆነ የዕድሜ ባለፀጋ አዛዉንቶች ይናገራሉ፡፡ክልሉም በሶስት/3/ ዞኖች፣በአንደ/1/ከተማ አስተዳደር፣ በአንድ/1/ ልዩ ወረዳና በሃያ/20/ ወረዳዎች እንዲሁም በአራት መቶ ሰባ ሰባት/477/ ቀበሌዎች የተዋቀረ ነዉ፡፡ ሶስቱ ዞኖችና ከተማ አስተዳዳርም አሶሳ ዞን፣መተከል ዞን፣ ካማሺ ዞንና አሶሳ ከተማ አስተዳደር ሲሆኑ በአሶሳ ዞን ስር ሰባት/7/ ወረዳ፣ በመተከል ዞን ስር ሰባት/7/ ወረዳ፣በካማሺ ዞን ስር አምስት/5/ ወረዳና በአሶሳ ከተማ አስተዳደር ስር ሁለት/2/ወረዳዎች አላቸዉ፡፡ ይህም ክልል በምዕራብ ሱዳን፣በምሥራቅና በደቡብ የኦሮሚያ ክልል፣በደቡብ የጋምቤላ ክልልና በሰሜንና ሰሜን ምሥራቅ የአማራ ብሄራዊ ክልል መንግሥት ያዋሱኑታል፡፡50.381 ስኩዌር ኪ.ሜ የቆዳ ሥፋት ያላት ሲሆን ከዚህም ውሥጥ ቆላ 91.86%፤ወይናደጋው 7.91 % እናደጋው 0.19% የሚሸፍን የአየር ንብረት ያለው ክልል መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ:: የክልሉ ዓመታዊ አማካይ የሙቀት መጠን 22.4 ሲሆን 1401.2 .ሜ የሚደርስ ደግሞ ዓመታዊ አማካይ የዝናብ መጠን እንዳለው ከኢትዮጵያ ሜትዮሮሎጅ ኤጀንሲ አሶሳ ቅርንጫፍ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡

የክልሉ ህዝብ ብዛት በ1999 በተካሄደዉ ህዝብና ቤት ቆጠራ መነሻነት በ2009 ዓ.ም1,065,938 ሲሆን የገጠር ህዝብ ብዛት ደግሞ 836,001 ሆኖ ከዚህ ዉስጥ በገጠር የሚኖር አርሶ አደር የአባ/እማ ቁጥር 181,698 እና በግብርና ስራ የሚተዳዳሩት ደግሞ 220,668 (92.5 በመቶ) አባ/እማ ወራዎች ናቸዉ፡፡

የክልሉ ህዝብ በሶስቱም የአየር ንብረት ክልሎች የሚኖር ሲሆን አብዛኛዉ ህ/ሰብ በቆላማ የአየር ንብረት(75 በመቶ ቆላ/በ1500 ከፍታ በታች) ክልል ዉስጥ የሚኖርና የኑሮ መሰረቱም እርሻ ሆኖ በተጨማሪ በእንስሳት እርባታ(በጥምር ግብርና) ይተዳደራል፡፡ ከእርሻ ስራ ዉጭ የሆኑ የግብርና ስራዎችም እንደ ንብ ማነብ፣አሳ ማስገር፣ባህላዊ ወርቅ ቁፋሮና አነስተኛ የጠረፍ ንግድ የኑሮ መዶጎሚያ በመሆን ያገለግላሉ፡፡ አብዘኛዉ የክልሉ ህዝብ አርሶ አደር ሲሆን ከ92.5 በመቶ የሚሆነዉ ህዝብ በግብርና ስራ የሚተዳደርና ሰፊዉን የስራ ዕድል ፈጥሮ ያለ ዘርፍ ነዉ፡ 
ከተለያዩ የመንግስት አካላት ጋር በምን መልኩ መገናኘት ይመርጣሉ?