አማርኛ

የቢሮው ዕሴቶች

በመንግሥት የኮሙዩኒኬሽን ሥርዓት ግንባታ ውስጥ የመሪነት ሚና እንጫወታለን፤

ተቋማችን በአዋጅ ሲቋቋም ከተሰጠው ተልዕኮ ውስጥ ዋነኛው በመንግስት ኢንፎርሜሽንና ኮሙኒዩኬሽን ውስጥ የመሪነት ሚናን መጫወት ስለሆነ የተቋማችን ዋና እሴት አድርገን ወስደነዋል፡፡

ግልፀኝነት

ግልፀኝነት በትክክል የሚሰራ ዲሞክራሲ መገለጫ ነው፡፡ ግልጸኝነት ለህዝቡ በቅርበት መረጃ መስጠትን ፣ ህዝብን ማድመጥንና ሀሳቡን በነፃነት እንዲገልፅ ማድረግን ፣ ጠቃሚ መረጃዎችን ህዝቡ ከመጠየቁ አስቀድሞ ተደራሽ ማድረግን ፣ ህዝባዊ ውይይቶችን በማድረግ ህዝቡ መረጃ እንዲኖረው ማድረግን ፣ ድጋፍ የሚሹ የማህበረሰብ ክፍሎችን በመረጃ ተደራሽ ማድረግን ያካትታል፡፡

ተጨባጭ እውነታ ላይ መመስረት

ለህዝቡ የምናቀርበው መረጃ ታማኝ ሊሆን የሚችለው በተጨባጭ እውነታ ላይ የተመሰረተና በአገባቡ ሲሆን ነው፡፡ የመግባቦት ስራ ከመንግስት ተቋማት ሃላፊነትና ተግባር አንፃር መሆን አለበት፡፡ ምናስተላልፈው መልዕክትና መልዕክቱን የምናስተላልፍበት መንገድ ከማህበረሰቡ ፍላጎትና እውቀት አንፃር መቃኘት አለበት፡፡

ይህ ማለት፤

· የምንጠቀመው ቋንቋ ግልፅና በቀላሉ መረዳት የሚቻል መሆን አለበት

· የመግባቦቱ ትኩረት ፓሊሲዎችን ማሳወቅን፤ ፖሊሲዎች ሊያመጡ የሚችሉትን ልማትና ውጤታማ ሊሆኑ የሚችሉት በተባበረ የመንግስትና የህዝብ ጥረት መሆኑን ማስረገጥ ይኖርብናል፡፡

ወቅታዊነት

የመንግስት ኮሙኒኬሽን ስራ ወቅታዊና ተቋሙ ቅድሚያ መስጠት ለሚገባቸው ስራዎች ቅድሚያ በመስጠት መከናወን ይኖርበታል፡፡ የህዝብና የመንግስት መረጃዎች ወቅታቸው ካለፈ ጥቅም ላይ መዋላቸው ፋይዳ አይኖረውም፡፡ ስለሆነም መረጃዎቹ በወቅቱ ተሰብስበውና ተተንትነው ለሚመለከተው አካል በወቅቱ እንዲደርሱ መድረግ ከተቋማችን ዋና ዋና እሴቶች አንዱ ይሆናል

ህዝባዊነት

በዲሞክራሲ ስርዓት የሚመራ መንግስት እንደመሆናችን መጠን የሉዓላዊ ስልጣን ባለቤቶች ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ናቸው፡፡ የህዝቡን ፍላጎቶች እያሟላን ስንሄድ ብቻ ነው ህዝቡ ይሉኝታዉን ሊሰጠን የሚችለው፡፡ ስለሆነም እንደ ህዝብ አገልጋይነታችን ህዝቦን ማዳመጥ፤ ነፃ የመረጃ አቅርቦት እንዲያገኝና ፍላጎቱን ለማሟላት እንተጋለን፡፡ ለህዝብ ጥያቄዎችና ምላሾቻቸው ትልቅ ዋጋ እንሰጣለን::

ፈጠራ እና መማማር

የኮሚኒኬሽንና ሚዲያ ስራ በክልላችን በደንብ ያልዳበረ እንደመሆኑ መጠን አዳዲስ ሀሳቦችንና አሰራሮችን ከተጨባጭ ተግባራትና ከነባራዊ ሁኔታችን አንፃር ማፍለቅ፤ ማወቅና መማር ይገባናል፡፡ ምርጥ ተሞክሮዎችን መቀመርና ማስፋትም ተገቢ ስለሚሆን አንዱ እሴታችን ይሆናል፡፡

የቡድን ስራ

ስራችንን በቡድን ተደራጅተን በቅንጅት ከሰራን ውጤቱ ከፍተኛ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ በቡድን ስራ ውስጥ መደጋገፍና መማማር ይቻላል፡፡ ስራን መከፋፈልና ውጤቱን በጋራ መገምገምም የዚሁ አካል ይሆናል፡፡ ስለሆነም ስራችንን በቡድን ተከፋፍለን በለውጥ ሰራዊት መልክ መተግበር ሌላኛው እሴታችን ይሆናል፡፡

ጥራት፤ ቅልጥፍና እና ውጤታማነት

ጥራት ያለው መረጃን በተለያዩ የመገኛኛ ብዙሀን አውታሮች ለህዝቡ ማድረስ የጠበቅብናል፡፡ የምንሰራው ስራ ወጪ ቆጣቢና ወቅታዊም መሆን ይጠበቅበታል፡፡ የስራችንን የመጨረሻው ማጠንጠኛ ውጤት መሆኑን በመገንዘብ ከላይ የተጠቀሱት ጥራት፤ ቅልጥፍናና ውጤታማነት እሴቶቻችን አድርገንለተግባራዊነታቸው እንተጋለን፡፡

 

 

 
ከተለያዩ የመንግስት አካላት ጋር በምን መልኩ መገናኘት ይመርጣሉ?