አማርኛ

የቤ////ግብርና ቢሮ በአሁኑ ወቅት፡- “2017 በገበያ የሚመራ ዘመናዊ ግብርና፣ ከድህነት የተላቀቀ እና መካከለኛ ገቢ ያለው ህብረተሰብ ተፈጥሮ ማየትራዕይ ሰንቆ እየሰራ ይገኛል፡:


የክልሉ ግብርና ቢሮ የሰብል ምርትና ምርታማነትን በመጠን ፣በጥራት እና በአይነት ማሳደግ ፣የተፈጥሮ ሀብትን በዘላቂነት ማልማት ፣መጠበቅና ለጥቅም ማዋል እንዲሆም የምግብ ዋስትናን የማሳደግና ለአዳጋ ጊዜ የምግብ ክምችትን ማሟላት ተቀዳሚ ተግባራቶቹ አድርጎ የሚሰራ ተቋም ነው፡፡


የግብርና መር ኢንዱስትሪ እቅድ እውን በማድረግ ግብርናችንን ወደ ላቀ ደረጃ እናደርሳለን !!

የመረጃ ምንጭ -የግብርና ቢሮ የህ//ዳይሬክቶሬት

ተልዕኮ(Mission)
የክልሉን ተፈጥሮ ሀብት በማልማት፤ አርሶአደሩ ከሥነ-ምህዳር ጋር የተጣጣመ የተሻሻሉ የግብርና ግብዓትና ቴክኖሎጂዎችን እዲጠቀም በማድረግ፤ የተቀናጀ የግብርና ኤክስቴንሽን ምክር አገልግሎት ለአርሶአደሩና ለግል ባለሀብቱ በመስጠት፤ በተግባር በተደገፈ ስልጠና አመለካከቱ የተቀየረ፤ ዕውቀትና ክህሎት ያለው የተማረ አርሶ አደር በማፍራት ገበያን ተኮር ባደረገ አመራረት የግብርና ምርትና ምርታማነት በማሳደግ የአ/አደሩ ኑሮ እንዲሻሻል ማድረግ፡፡

እሴት

  • የህዝብ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን እናረጋግጣለን!

  • የሰው ሀይል ልማትን ለተማዊ ስኬት እናውላለን!
  • ቀጣይ እድገትን ለማረጋገጥ የማያቋርጥ ለዉጥን ባህላችን እናደርጋለን!
  • ድህነትን ታሪክ እናደርጋለን !
  • ለመልካም አስተዳድር መርሆች እንገዛለን!
  • ተገልጋይን ለማርካት ተግተን እንሰራለን !

 

 

 

 

 

 
ከተለያዩ የመንግስት አካላት ጋር በምን መልኩ መገናኘት ይመርጣሉ?