አማርኛ
Article Index
ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ፣
መግቢያ
All Pages

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ 2010 በጀት አመት የስድስት ወር የስራ አፈጻጸምን የያዘ መረጃ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽ ቢሮ ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ እሴቶች

ተልዕኮ

ለከተማዉ ማህበረሰብና ለከተማዉ ነዋሪ አመቺ ከባቢያዊ ሁኔታን በመፍጠር ግልፅ እና ቀልጣፋ አገልግሎቶችና ድጋፍ በመስጠት ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን እንዲስፋፋና እንዲጐለብቱ በማድረግ በክልሉ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገት እንዲመጣ ማድረግ፡፡

ራዕይ

2012 . በክልሉ ከተሞች ዘላቂ ልማትና መልካም አስተዳደር በማስፈን ለነዋሪዎች ምቹ እና ሀገር አቀፍ ደረጃዉን የጠበቀ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ተፈጥሮ ማየት፡፡"

እሴቶች /core values/

ዘርፉ የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት በብቃት ለመወጣትና በክልሉ ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ሊያበረክት የሚገባውን አስተዋጽኦ በስራ ሂደቱ አፈጻጸምም ሆነ በፈጻሚዎቹ የስራ ዲሲፕሊን ዙሪያ የዕለት ከዕለት ተግባሩ በሚከተሉት እሴቶችና የአሰራር መርሆዎች ላይ የተመሰረተ ይሆናል፡-

o ደንበኛን ለማርካት ጠንክረን እንሰራለን!

o ሙስናን እንፀየፋለን!

o ህብረተሰቡ በተደራጀ አግባብ የልማት ተጠቃሚ እንዲሆን ጠንክረን እንሰራለን!

o ጥራትና ቅልጥፍና መገለጫችን ነው!

o በቡድን አሰራር እናምናለን!

o ለመማማርና ለለውጥ ዝግጁነን!

o ቁጠባ ባህላችን ነው!

o በውጤት እናምናለን!

o የስራ ፍቅር፣ ከበሬታና መልካም ስነ-ምግባር እናጎለብታለን!

o በፌዴራልና በክልሉ የሚወጡ የሴክተር አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎችን ጠንቅቆ በማወቅና አቅም በማዳበር ፍትሐዊነት የተሞላበት አሠራር ማስፈንን ዋነኛ መለያ እሴቶቹ አድርጐ ይንቀሳቀሳል፡፡

የመሥሪያ ቤታችን አበይት ዋና ዋና ተግባራት እና የትኩረት ቅደም ተከተላቸው

o የከተማ ሥራ ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ማጠናከር፣

o የከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ሥርዓት ማዘመን፣

o የከተማ የመኖሪያ ቤቶች አቅርቦት ማመቻቸት፣

o የከተሞች መልካም አስተዳደር ማጠናከርና የማስፈጸም አቅም ግንባታን ማፋጠን፣

o የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ልማት ማጠናከር፣

o የከተሞች መሠረተ-ልማት ማስፋፋት፣ እና የከተሞች ጽዳትና አረንጓዴ ልማት ማጠናከር ናቸው፡፡

የቢሮው ሥልጣንና ኃላፊነት (Mandate)

የክልሉን መንግስት አስፈፃሚ አካላት አደረጃጀት፣ሥልጣንና ተግባር መወሰኛ አዋጅ ቁጥር 94/2003 . ማሻሻል በማስፈለጉ የቤ//// የአስፈፃሚ አካላት አደረጃጀት፣ ሥልጣንና ተግባራቸዉን እንደገና ለመወሰን በወጣ አዋጅ ቁጥር 129/2008 . በአዋጁ አንቀጽ 16 መሠረት ለከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ

የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-

o የከተማና የገጠር ትስስር እና የከተሞች የእርስ በርስ ትስስር እንዲጠናከር ስትራቴጂ ይቀይሳል ተግባራዊ ያደርጋል፤

o አግባብ ባለዉ ህግ የክልሉን የከተማ መሬት አሰ/ ስርዓትን ያስፈጽማል፣ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣ የከተማ መሬት አቅርቦትና አስ/ ሥርዓት ይዘረጋል፤

o የከተማ ምግብ ዋስትና ፕሮግራምን በባለቤትነት ያስተባብራል፣ ከሚመለከታቸዉም አካላት ጋር በመቀናጀት ይደግፍል፣ አፈፃፀሙንም ይከታተላል፣ ዘላቂነት ካለዉ የልማት ተግባር ጋርም ያስተሳስራል፤

o ከተሞችን የደረጃ መመዘኛና ደረጃ ይወስናል፣ ዕዉቅና እንዲያገኙ ያደርጋል፤

o ከተሞች የአካባቢያቸዉን የልማት ማዕከል እንዲሆኑ የተቀናጀ ድጋፍ ይሰጣል፤

o የከተሞች ልማት ከገጠር ልማት እና ከድህነት ቅነሳ ጋር በተቀናጀ መንገድ የሚከናወንበትን ሁኔታ በሚመለከት ጥናት ያደርጋል፣ ተግባራዊ እንዲሆን ያግዛል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤

o በከተሞች ዘመናዊ መሰረተ-ልማት እንዲሲፋፋ ጥረት ያደርጋል፣ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚዉል የለማ መሬት ያዘጋጃል፤

o የክልሉን ከተሞች ፕላን ያዘጋጃል፣ አተገባባራቸዉን ይከታተላል፣ ድጋፍ ይሰጣል፤

o በከተማ ፕላን ዝግጅት ለሚሰማሩ አማካሪዎች የብቃት ማረጋገጫ ይሰጣል ደረጃቸዉን ይወስናል፣ ፈቃድ ይሰጣል፣ ይሰርዛል፤

o ከተሞች ከሚያመጯቸዉን ደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻዎች የሚወገዱበትንና ዉበት ያላቸዉ የመናፈሻ አገልግሎቶች የሚመሰረቱበትን የአሰራር ሥርዓት ይዘረጋል፣ ድጋፍ ያደርጋል፤

o በከተሞች ለህዝብ ልማት ሲባል ለመንግሥታዊ ፕሮጀክቶችና ለሌሎች አገልግሎቶች ለሚዛወሩ ይዞታዎችና ከይዞታቸዉ ለሚፈናቀሉ ሰዎች ካሳ የሚከፈልበት ሥርዓት እንዲዘረጋ ያደርጋል አፈፃፀሙን ይከታተላል፤

o ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚዉል የለማ መሬት ያዘጋጃል፣ ለተገልጋይ ያቀርባል፣ የአቅርቦቱን ፍትሀዊነት ያረጋግጣል፣ የተላለፈዉ መሬት ህጋዊነት ተከትሎ ለልማት መዋሉን ይከታተላል፣ ህገ-ወጥ ግንባታዎችን ይቆጣጠራል፣ ህጋዊ ሥርዓትን ያስይዛል፤

o የመሬትና የንብረት ዋስትና ካሳ ሥርዓት ይዘረጋል፤

o በቴክኖሎጂ የተደገፈ ወጥ የሆነ የከተማ መሬት ይዞታ ምዝገባና የአድራሻ መረጃ ሥርዓት በክልሉ ይዘረጋል፤

o በከተሞች የልማትና መልካም አስ/ ሥራዎች ላይ ነዋሪዉን ህዝብ በተደራጀ አግባብ እንዲሳተፍ ለማስቻል የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል፣ የማስፈፀም አቅም ይገነባል፣ ያስተባብራል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤

o በክልሉ የሚካሄደዉን የቤቶች ልማት ፕሮግራሞችን ይመራል፣ የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል፣ ይቆጣጠራል የከተማ ነዋሪ ህዝብ ከአቅሙ ጋር የተመጣተነ የመኖሪያ ቤት እንዲሰራ ስልት ይቀይሳል፣ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፤

o የፌዴራልና የክልሉ መንግሥት የግንባታ ኮዶች፣ ስታንደርዶችን ህጎች መከበራቸዉን ያረጋግጣል፣ የዲዛይንና የግንባታ ሥራዎችን ደረጃ ይወስናል፤

o በግንባታ ዘርፍ ለሚሰማሩ የምህንድስና ባለሙያዎች፣ አማካሪዎችና ሥራ ተቋራጮች ይመዘግባል የሙያ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ይሰጣል፣ ያድሳል፣ ይሰርዛል፤

o በክልሉ መንግስት ለሚገነቡ ህንፃዎች የዲዛይንና የግንባታ ዉሎች ስለሚይዟቸዉ የዉል ቃሎችና የቴክኒክ መመሪያ ያዘጋጅል፣ በተገባዉ ዉል መሠረት የጥራት ደረጃቸዉን፣ የጊዜና የዋጋ ገደቦች ተጠብቀዉ መሰራታቸዉን ይቆጣጠራል፣ አስፈላጊዉን ድጋፍ ይሰጣል፣ እርምጃ ይወስዳል፤

o በክልሉ መንግሥት ለሚካሄዱ ግንባታዎች ዲዛይን ያዘጋጃል፣ የዋጋ ጥናት ያካሂዳል፣ የምህንድስና ግምት ያዘጋጃል፣ ተግባራዊ መሆኑን ያረጋግጣል፣ በዉለታዉ መሠረት መፈፀሙን ይከታተላል፤የጥራት ቁጥጥር ያደርጋል፤

o የኮንስትራክሽን ግብዓት በላብራቶሪ እየተፈተሸ ለግንባታ አገልግሎት መዋሉን ያረጋግጣል፤

o የክልሉን የኮንስትራክሽን የዲዛይን ሥራዎች ፍላጎት ያጠናል፣ ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፤

o አግባብ ላለዉ አካል በህግ የተሰጠዉን ሥልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ የኮንስትራክሽን ሥራ ደረጃዎች ያወጣል፣ መከራቸዉንም ይከታተላል፤

o የኮንስትራክሽን ዘርፍን እንቅስቃሴ ይመራል፣ አፈፃፀሙንም ይከታተላል፤

o በአማካሪዎች ወይም በሌላ አካላት ለሚሰማሩ ዲዛይኖች የማወዳደሪያ ዝክረ ተግባር ያዘጋጃል፣ አማካሪ ደረጃ ይወስናል፣ የአማካሪዎችን ወርሃዊ የግንባታ ሂደት ሪፖርት ይገመግማል፣ የአገልግሎት ክፍያቸዉን ያፀድቃል፤

o በአማካሪዎች ወይም በሌላ አካል የተሰሩ ዲዛይኖችን ይመረምራል፣ያፀድቃል፣ የግንባታ ክትትል ቁጥጥር ሥራዎችን የካሂዳል፣ ክፍያዎችን ያፀድቃል፤

o የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ልማትና የቁጥጥር ሥራዎችን ያከናዉናል፤

o የዘርፉን የሰዉ ሀብት ልማትና ደረጃዎች ዝግጅት ሥራዎችን ተግባራዊ ያደርጋል፣ የሚመለከታቸዉን አካላትም ያስተባብራል፤

o በመንግሥትም ሆነ በግል ተቋማት በህንፃ አዋጁ በተካተቱ እና ወደፊትም በሚካተቱ ከተሞች ለሚገነቡ ህንፃዎች ዲዛይን ይገመግማል፣ የግንባታ ፈቃድ እና የመጠቀሚያ ፈቃድ ይሰጣል፤

o የህንፃ ሹም /ቤቶችን ያደራጃል፣ ይመራል፣ ይቆጣጠራል፣ የግንባታ ግብዓት ጥናትና ምርምር ያካሂዳል፣ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን በጥናትና ምርምር ሥራዉ እንዲሳተፍ ያስተባብራል፤

o በክልሉ የዲዛይንና የኮንስትራክሽን ዘርፍ ለተሰማሩ አማካሪዎች፣ ኮንትራክተሮች እና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ሥራዎችን ያከናዉናል፤

o በግንባታ ሥራ ሰፊ የሥራ ዕድል እንዲፈጠር ግንባታዎች ጉልበት ተኮር እንዲሆኑ ያበረታታል፤

o ዓላማዉን ለማስፈፀም የሚረዱ ሌሎች ተግባራትን ያከናዉናል፤


 
ከተለያዩ የመንግስት አካላት ጋር በምን መልኩ መገናኘት ይመርጣሉ?