አማርኛ

 

የቤ/ጉ/ክ/መ/የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን

ተልዕኮ (Mission)

በክልሉ ሙስናና ብልሹ አሠራር በመከላከል፣ የሙስና ወንጀልን በመመርመር፣ በመክሰስ፣ ግልጸኝነት እና ተጠያቂነት አሠራርን በማስፈን የክልሉ ሀብት ለልማት እንዲውል ማድረግ፡፡

ራዕይ (Vision)

በክልሉ ብልሹ አሠራር ለመልካም አስተዳደር እና ለልማት እንቅፋት ከማይሆንበት ደረጃ ደርሶ ማየት፡፡

 

 

 

የተከበሩ አቶ ብርሀኑ አየሁ

የቤ/ጉ/ክ/መ/የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር

 

 

 

የቤ/ጉ/ክ/መ/የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሙስና ወንጀልና ብልሹ አሠራር ለልማትና ለመልካም አስተዳደር የሚያስከትሉትን ተፅዕኖ በእጅጉ ለመቀነስ መሠረታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በትኩረት ይሠራል፡፡ ማስተማር፣ መከላከልና ህግ ማስፈፀም፡፡ ዜጐች በመልካም ሥነ-ምግባር እንዲታነፁ ከሙስና ወንጀልና ብልሹ አሠራር ተግባራት እራሳቸውን እንዲያርቁ የማስተማር ስራ በስፋት ይከናወናል፡፡

የሙስና ወንጀልና ብልሹ አሠራር ከመከሠቱ በፊት ወንጀሉ ሊፈጠርባቸው የሚችሉ የስጋት ምንጮችን እየለዩ የማድረቅ ስራዎች በተከታታይነት ይሠራሉ፡፡ የመንግስት ተቋማትና በመንግስት የልማት ድርጅቶች የሚታዩ የአሠራር ክፍተቶች በአሠራር ስርዓት ጥናት ይዳሠሳሉ፡፡ በጥናቱ ግኝቶች ላይ በሚሠጡ የመፍትሄ እርምጃዎች መሠረት ተቋማት አሠራሮቻቸውን እንዲያሻሽሉ፣ ወደ ሙስና የሚወስዷቸውን ክፍተቶች እንዲያርሙ የድጋፍና የማማከር አገልግሎት ይሠጣቸዋል፡፡

የፀረ-ሙስና ትግሉ ህዝባዊ መሠረት እንዲኖረው የስነ-ምግባር አውታሮችን የማደራጀት፣ የመደገፍና የማጠናከር ስራ በስፋት እየተከናወነ ይገኛል፡፡ የመንግስት አሠራር ግልፀኝነትና ተጠያቂነት የሠፈነበት እንዲሆን በማድረግ በህዝብና በመንግስት አሠራር ላይ የጥቅም ግጭት እንዳይከሠትና መተማመን እንዲኖርም የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ስራ ዘርግቶ ወደ ተግባር ገብቷል፡፡ ይህ አንዱ የሙስና ወንጀል መከላከያ ከመሆኑም ባሻገር ህዝብ በመንግስት ላይ አመኔታ እንዲፈጥር ከሚያስችሉ ስልቶች አንዱ ነው፡፡

የትምህርትና መከላከል ስራዎችን ተከትሎ ህግ የማስፈፀም ስራ ይከናወናል፡፡ የሙስና ወንጀል የፈፀመ ማንኛውም ግለሠብ በሠራው ወንጀል ይጠየቃል፡፡ የሙስና ወንጀል ስለመሠራቱ ሙከራውና አዝማሚያው ስለመኖሩ ለኮሚሽኑ ጥቆማ ሲሠጥ ወይም ኮሚሽኑ በራሱ ተነሳሽነት በሚሠራው ስራ ተፈፅሟል በተባለ የሙስና ወንጀል ላይ ተገቢው ምርመራ በማስረጃ በማሠባሠብ ስራ በተሟላ ጥንቃቄ ይፈፀማል፡፡ ክስ ተመስርቶ በተፈፀመው ወንጀል ልክ መሠረት ተገቢውን ቅጣት እንዳያገኝ ይደረጋል፡፡ ወንጀለኞችን ከመቅጣቱ ሥራ ጐን ለጐንም የፍትሐ ብሄር ክስ መስርቶ በመከራከር በሙስና የተመዘበረ የሙስና የወንጀል ፍሬ የሆነ የመንግስትና የህዝብ ሀብት እንዲመለስ የፍትሐ-ብሄር ክስ ክርክር ተደርጐ የወንጀሉ ፍሬ ለመንግስት የሚመለስበት ሁኔታ ያመቻቻል፡፡ በመሆኑም ህግ የማስፈፀም ስራ ሶስተኛው የኮሚሽኑ ስራ ዘርፍ ነው፡፡

ሙሰኞች ከህዝብ እይታ አይሰወሩም፤ ከህግም አያመልጡም!

Corruptions are under the watchful Eyes of the public!

ለሙስና ወንጀልና ለብልሹ አሠራር ጥቆማ

ስ.ቁ - ዐ57 - 775 - 1772

ፓ.ሳ.ቁ - 25 አሶሳ

ፋክስ - ዐ577752421

Face book page - የቤ/ጉ/ክ/መ/የሥነ-ምግባርናና ፀረ ሙስና ኮሚሽን

 

 
ከተለያዩ የመንግስት አካላት ጋር በምን መልኩ መገናኘት ይመርጣሉ?