አማርኛ
Article Index
ክልል ምክር ቤት ጽህፈት ቤት፣
ተልዕኮ፣ራዕይና እሴቶች
ተግባርና ኃላፊነት
All Pages

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ክልል /ቤት የክልሉ መንግስት ህግ አውጭ አካል ከፍተኛ የስልጣን ባለቤት መሆኑ በተሸሻለው የክልሉ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 49 ንዑስ አንቀጽ 1 እና 2 በተገለጸው መሰረት /ቤቱ 99 መቀመጫዎች እንዲኖሩት ሆኖ ተደራጅቷል፡፡

በዚህ መሠረት /ቤቱ የክልሉን የሠላም፣ልማት፣መልካም አስተዳደርና የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ሂደት የሚያሳልጡ ሕጐችን ማውጣት፣ በየደረጃው ያሉ የመንግሥት አስፈጻሚ አካላት ዕቅድ አፈፃፀምን መከታተልና መቆጣጠር፣ የሕዝብ ውክልና ኃላፊነትን በተገቢው ሁኔታ መወጣት እና የክልሉን መንግሥት የዕለት ከዕለት ተግባራት የሚያስተባብሩ ብሎም የሚመሩ የሥራ ኃላፊዎችን ሹመትና ከሹመት የመነሳት ጥያቄ መርምሮ ውሣኔ ማሳለፍን ጨምሮ ሌሎች ተግባትን ያከነውናል፡፡

ከእነዚህ ዓበይት ተግባራት ጐን ለጐንም የም/ቤቱን አባላትና አካላት /ቤታዊ ግንዛቤ የማስፋት፤ በአሠራር ሥርዓቱ መሠረት በሥልጣን ገደቡ ውስጥ የሚወድቁ የሕዝብ አቤቱታዎችንና ቅሬታዎችን በመቀበል በሚመለከታቸው አካላት በኩል ምላሽ እንዲያገኙ የማድረግ፤ የተዋረድ /ቤቶችን አፈፃፀም በቅርበት የመከታተልና የማጠናከር፤ ብሔራዊ በዓላትን በተለይም የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እንዲሁም የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓላትን በበላይነት የማስተባበርና የመምራት ኃላፊነቶች እየተወጣ ይገኛል፡፡

ምክርቤቱ የተለያዩ ሕጐችን በማውጣት፣ የአስፈፃሚውንም ሆነ የዳኝነት አካሉን አሠራር በመከታተል፣ በመቆጣጠርና ተገቢውን የማስተካከያ አቅጣጫ በመስጠት ዕቅዶቻቸው በሕዝብ የላቀ ተሳትፎ ከግብ እንዲደርሱ ከማስቻልና እንደ ክልል ግልፀኝነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት የአሠራር ሥርዓት ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት ከማፋጠን ባለፈ የክልሉን ሕዝብ ቀጥተኛ ተሳታፊነትና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት በማሳደግ ረገድ እንዲሁም በሥራ ክንውን ወቅት ያጋጠሙትን ዓበይት ተግዳሮቶችና በቀጣይ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ጉዳዮች ይመለከታል ጉባኤ ላይ ቀርበው እንዲፀዲቁ ያደርጋል፡፡

ክልሉ በየዕቅድ ዘመኑ አስፈጻሚው አካል፣የጣላቸውን ግቦች ለማሳካት፣ ስኬቶቹንም ዳር ለማድረስ፣ የሕዝቡን የሠላም፣ የልማትና የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ተሳታፊነትና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችል አስተዋጽዖ በማበርከት ልማትን ለማፋጠን ይተጋል፡፡

 

 


የክልል ምክር ቤት ተልዕኮ፣ራዕይና እሴቶች

 

ተልዕኮ (Mission)

በክልሉ የተለያዩ ሕጐችን በማውጣት፣ የሕጐችን አፈጻጸም በመከታተል፣ በመቆጣጠር፣ በመመርመር የሕዝብ ውክልናን በብቃት በመወጣት የሕግ የበላይነት የተረጋገጠበትና መልካም አስተዳደር የሰፈነበት ክልል ለመገንባት በቁርጠኝነት መሥራት ነው፡፡

ራዕይ (Vission)

2017 / የክልሉ ሕዝብ የልማት፣የዴሞክራሲ ስርዓትና መልካም አስተዳደር በላቀ ደረጃ ተጠቃሚ ሆኖ ማየት፡፡

እሴቶች /values/

1. የሕግ የበላይነትን እናከብራለን

2. ሕገ-መንግሥታዊ መብቶችን እናከብራለን፣

3. ተጠያቂነት፣ግልፀኝነትና አሣታፊነት አሠራር እንዘረጋለን፣

4. የሕዝቡን ጥቅምና መብት እናስቀድማለን፣

5. ራዕያችንን እውን ለማድረግ በቁርጠኝነት እንሠራለን፣

6. ሙስኝነትና ብልሹ አሠራርን እንታገላለን፣

የምክር ቤቱ፣ የቋሚ ኮሚቴዎችና የጽ/ቤቱ ተግባርና ኃላፊነት

የምክር ቤቱ ስልጣንና ተግባር

የክልሉ ምክር ቤት በተሻሻለዉ የክልሉ ህገ-መንግስት አንቀጽ 49 መሰረት የክልሉ ህግ አውጭ አካልና በዉስጥ ጉዳዮች ከፍተኛ የፖለቲካ ሥልጣን ባለቤት ሲሆን በህዝቡ የተጣለበትን ከፍተኛ ኃላፊነት ለመወጣት የሚከተሉት ተግባራት ተለይተዉ ተሰጥተዉታል፡፡

· የፌዴራሉን ህገ-መንግስትና ሌሎችን ህጎችን የማይፃረር ልዩ ልዩ ህጎችን ያወጣል፣

· የህዝቡን ብዛት፣ የክልሉን ስፋትና ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴን ግምት ውስጥ በማስገባት በክልሉ ውስጥ ተጨማሪ የአስተዳደር እርከኖችን ወይም የራስን በራስ አስተዳደር አካባቢዎችን በህግ ያቋቁማል፣

· የፌዴራል መንግስት ስልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ ከአጎራባች ብሄራዊ ክልላዊ መንግስታት ጋር የሚያደርጉ ስምምነቶችን ያፀደቃል፣

· የራሱን አፈ-ጉባኤና ምክትል አፈ-ጉባኤ ይመርጣል፤ ለምክር ቤቱ ስራ የሚያሥፈልጉትን ቋሚና ጊዜያዊ ኮሚቴዎችን ይሰይማል፤

· ከምክር ቤቱ አባላት መካከል ርዕስ መስተዳደሩን በምርጫ ይሰይማል፤ በርዕስ መስተዳደሩ አቅራቢነት ክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት አባላት ሹመት ያጸድቃል፤

· በርዕሰ መስተዳድሩ አቅራቢነት የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት፣ ምክትል ፕሬዝዳንት፤ ዋና ኦዲተሩንና ምክትል ዋና ኦዲተሩን ይሾማል፣

· የክልሉ ጠቅላይ /ቤት፤ከፍተኛና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶችን ያቋቋማል፤ዳኞችን ይሾማል፣

· የኦዲትና ሌሎችንም የቁጥጥር አካላትን ያቋቁማል፤

· የክልሉን ሠላምና ፀጥታ ለመጠበቅ የሚያስፈልጉ መመሪያዎችን ያወጣል፤ የፀጥታንና የፖሊስ ኃይሎችን ያቋቁማል፤

· ክልሉን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፕሮግራሞችን ያፀድቃል፤

· የክልሉን የገቢ ምንጮችን የሚመለከቱ ህጎችን ያወጣል፤ የክልሉን በጀት ለብሄረሰብ ምክር ቤቶች፣ ለአስተዳደራዊ እርከኖችና ወረዳዎች በመቀመር ይመድባል፤ መርምሮ ያፀድቃል፡፡

· ለማህበራዊ አገልግሎት መስፋፋት፤ ለኢኮኖሚ ልማት መፋጠንና ለዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ አስፈላጊ የሆኑ ተቋማትን ያቋቁማል፤

· ለክልሉ መንግስት በተከለለው የገቢ ምንጭ በክልሉ ውስጥ የግብርና ታክሲ ይጥላል፤

· የክልል መስተዳደሩን ሰራተኛ አስተዳደርና የስራ ሁኔታዎችን በተመለከተ ህግ ያወጣል፤

· ለክልሉ መንግስት በተሠጠዉ ስልጣን መሰረት የአስችኳይ ጊዜ አዋጅ ያወጣል፤

· የሀገሪቱንና ክልሉ ህግጋተ መንግስታት አዋጆችና ሌሎች ህጎችን በክልሉ ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ ዝርዝር ማስፈፀሚያ ደንቦችን ያወጣል፤

· የክልሉን ርዕስ መስተዳደሩና ሌሎችንም የክልሉ መንግስት ባለስልጣናት ለጥያቄ ይጠራል፤ የአስፈፃሚውን አካል አሰራር ይመረምራል፡፡


የክልል ም/ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች ተግባርና ኃላፊነት /Mandate/፣

 

የፓርላማ ሥርዓት በሚከተሉ ሀገራት ም/ቤቶች የራሳቸዉን ቋሚ ኮሚቴዎች በማደራጀት የእለት ተእለት ሥራዎችን በተሳካ መልኩ እንደሚያከናውኑ ይታወቃል፡፡ በዚሁ መሰረት የቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልል ም/ቤት የም/ቤቱን ሥራዎች እንዲከታተሉ በአዋጅ ቁጥር 65/99 እና በደንብ ቁጥር 119/2010 መሠረት አምስት ቋሚ ኮሚቴዎችን በማደራጀት ተግባርና ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል፡፡

 

ቋሚ ኮሚቴዎችም በየዘርፋቸው ተለይተው የተደራጁ ሲሆን እነዚህም፡-

 

ሀ/ የሕግ፣ፍትህ አስተዳደር እና ፀጥታ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ

 

ለ/ ንግድ፣ኢንዱስትረና ከተማልማትና ኮንስትራክሽን ጉዳዩች ቋሚ ኮሚቴ፣

 

ሐ/ የሴቶች፣ሕፃናት፣ወጣቶች እና ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ

 

መ/ የግብርና አካባቢ ጥበቃ እና ተፈጥሮ ሀብት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ

 

ሠ/ የመንግስት በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዩች ቋሚ ኮሚቴ

 

ረ/ የሰው ሀብት ልማትና ማኅበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ናቸው፣

በተሻሻለው የምክር ቤቱ የአሰራርና የአባላት የሥነ-ምግባር ደንብ ቁጥር 119/2010 መሰረት ቋሚ ኮሚቴዎች የሚከተሉት የጋራ ስልጣንና ተግባራት አሏቸው፤

· የተመራለትን ረቂቅ ህግ በመመርመር ለም/ቤቱ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ ማቅረብ፣

· በመንግስታዊ አካላት ላይ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ፣

· ህግ ማመንጨት፣

· አቤቱታ ወይም ጥቆማ መቀበል፣

· ምስክሮችን መስማትና ሰነድ መመርመር፣

· በተቋቋሙበት አላማ ዙሪያ ጥናት ማካሄድ፣

· ልዩ ልዩ አውደ ጥናቶችና የውይይት መድረኮችን ማዘጋጀት፣

· የልምድ ልውውጥ ማድረግ፣

· ከም/ቤቱ ወይም ከአፈ-ጉባኤው የሚሰጠውን ሌሎች ሥራዎች ማከናወን የሚሉት ናቸዉ፡፡

የም/ቤቱ ጽ/ቤት ተግባርና ኃላፊነት፣

የክልሉ ምክር ቤት በተሻሻለው ህገ-መንግስት አንቀጽ 49 ተግባርና ሀላፊነት የተደነገገው እንዳለ ሁኖ የክልሉ ምክር ቤት ጽ/ቤት በአዋጅ ቁጥር 32/1995 አንቀጽ 5 የሚከተሉት ተግባርና ሀላፊነቶች አሉት፡-

1. ለም/ቤቱና ለቋሚ አካላቱ የጽህፈት አገልግሎት ይሰጣል ፤

2. ለም/ቤቱና ለቋሚ አካላቱ የመሰብሰቢያ አደራሽ ያዘጋጃል፣

3. ለም/ቤቱና ለቋሚ አካላቱ የቃለ-ጉባኤ ውሳኔዎችና ሠነዶች ተመዝግበው እንዲያዙና እንዲጠበቁ ያደርጋል፣

4. ለም/ቤቱና ለቋሚ አካላቱ የቤተ መጽሀፍት፣ ምርምርና የመረጃ አገልግሎት ይሰጣል፣

5. ም/ቤቱ የሚያወጣቸው አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎች በእንግሊዘኛ እንዲተሮገሙ፤ በልሳነ ህግ ጋዜጣ እንዲታተሙና ለሚመለከታቸው አካላትም ሆነ ለህ/ሰቡ እንዲያሰራጩ ያደርጋል፣

6. ም/ቤቱ የሚያወጣቸውን መጽሔትና ጋዜጣ ህትመትና ስርጭት ይከታተላል፤

7. የም/ቤቱን እንግዶች አስፈላጊውን የመስተግዶ አገልግሎት እንዲያገኙ ያደርጋል፤

8. የንብረት ባለቤት ይሆናል፣ ውል ይዋዋላል፣ይከሳል፣ ይከሰሳል፤

9. የም/ቤቱንና የቋሚ አካላቱን ሥራ ለማሰራት የሚረዱ ሌሎች ተግባሮችን ያከናውናል፣

 


 
ከተለያዩ የመንግስት አካላት ጋር በምን መልኩ መገናኘት ይመርጣሉ?