አማርኛ
Article Index
ክልል ምክር ቤት ጽህፈት ቤት፣
ተልዕኮ፣ራዕይና እሴቶች
ተግባርና ኃላፊነት
All Pages

የክልል ም/ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች ተግባርና ኃላፊነት /Mandate/፣

 

የፓርላማ ሥርዓት በሚከተሉ ሀገራት ም/ቤቶች የራሳቸዉን ቋሚ ኮሚቴዎች በማደራጀት የእለት ተእለት ሥራዎችን በተሳካ መልኩ እንደሚያከናውኑ ይታወቃል፡፡ በዚሁ መሰረት የቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልል ም/ቤት የም/ቤቱን ሥራዎች እንዲከታተሉ በአዋጅ ቁጥር 65/99 እና በደንብ ቁጥር 119/2010 መሠረት አምስት ቋሚ ኮሚቴዎችን በማደራጀት ተግባርና ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል፡፡

 

ቋሚ ኮሚቴዎችም በየዘርፋቸው ተለይተው የተደራጁ ሲሆን እነዚህም፡-

 

ሀ/ የሕግ፣ፍትህ አስተዳደር እና ፀጥታ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ

 

ለ/ ንግድ፣ኢንዱስትረና ከተማልማትና ኮንስትራክሽን ጉዳዩች ቋሚ ኮሚቴ፣

 

ሐ/ የሴቶች፣ሕፃናት፣ወጣቶች እና ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ

 

መ/ የግብርና አካባቢ ጥበቃ እና ተፈጥሮ ሀብት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ

 

ሠ/ የመንግስት በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዩች ቋሚ ኮሚቴ

 

ረ/ የሰው ሀብት ልማትና ማኅበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ናቸው፣

በተሻሻለው የምክር ቤቱ የአሰራርና የአባላት የሥነ-ምግባር ደንብ ቁጥር 119/2010 መሰረት ቋሚ ኮሚቴዎች የሚከተሉት የጋራ ስልጣንና ተግባራት አሏቸው፤

· የተመራለትን ረቂቅ ህግ በመመርመር ለም/ቤቱ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ ማቅረብ፣

· በመንግስታዊ አካላት ላይ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ፣

· ህግ ማመንጨት፣

· አቤቱታ ወይም ጥቆማ መቀበል፣

· ምስክሮችን መስማትና ሰነድ መመርመር፣

· በተቋቋሙበት አላማ ዙሪያ ጥናት ማካሄድ፣

· ልዩ ልዩ አውደ ጥናቶችና የውይይት መድረኮችን ማዘጋጀት፣

· የልምድ ልውውጥ ማድረግ፣

· ከም/ቤቱ ወይም ከአፈ-ጉባኤው የሚሰጠውን ሌሎች ሥራዎች ማከናወን የሚሉት ናቸዉ፡፡

የም/ቤቱ ጽ/ቤት ተግባርና ኃላፊነት፣

የክልሉ ምክር ቤት በተሻሻለው ህገ-መንግስት አንቀጽ 49 ተግባርና ሀላፊነት የተደነገገው እንዳለ ሁኖ የክልሉ ምክር ቤት ጽ/ቤት በአዋጅ ቁጥር 32/1995 አንቀጽ 5 የሚከተሉት ተግባርና ሀላፊነቶች አሉት፡-

1. ለም/ቤቱና ለቋሚ አካላቱ የጽህፈት አገልግሎት ይሰጣል ፤

2. ለም/ቤቱና ለቋሚ አካላቱ የመሰብሰቢያ አደራሽ ያዘጋጃል፣

3. ለም/ቤቱና ለቋሚ አካላቱ የቃለ-ጉባኤ ውሳኔዎችና ሠነዶች ተመዝግበው እንዲያዙና እንዲጠበቁ ያደርጋል፣

4. ለም/ቤቱና ለቋሚ አካላቱ የቤተ መጽሀፍት፣ ምርምርና የመረጃ አገልግሎት ይሰጣል፣

5. ም/ቤቱ የሚያወጣቸው አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎች በእንግሊዘኛ እንዲተሮገሙ፤ በልሳነ ህግ ጋዜጣ እንዲታተሙና ለሚመለከታቸው አካላትም ሆነ ለህ/ሰቡ እንዲያሰራጩ ያደርጋል፣

6. ም/ቤቱ የሚያወጣቸውን መጽሔትና ጋዜጣ ህትመትና ስርጭት ይከታተላል፤

7. የም/ቤቱን እንግዶች አስፈላጊውን የመስተግዶ አገልግሎት እንዲያገኙ ያደርጋል፤

8. የንብረት ባለቤት ይሆናል፣ ውል ይዋዋላል፣ይከሳል፣ ይከሰሳል፤

9. የም/ቤቱንና የቋሚ አካላቱን ሥራ ለማሰራት የሚረዱ ሌሎች ተግባሮችን ያከናውናል፣

 
 
ከተለያዩ የመንግስት አካላት ጋር በምን መልኩ መገናኘት ይመርጣሉ?