English
Important
LOGIN

(አሶሳ፣ ሚያዚያ 12/2011 .) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ለአርቲስት ወይኒቱ አንዱር የገንዘብ እና የድርጅት ቦታ ድጋፍ አደረገ።

አርቲስት ወይኒቱ አንዱር በተለይም በጥበብ ዘርፉ ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና ለሀገር የላቀ አስተዋጽዖ አበርክታለች።

አርቲስቷ በጉሙዝኛ፣ በሶማልኛ እና በኦሮምኛ ቋንቋዎች 30 በላይ የሙዚቃ ሥራዎችን ሠርታ ለህዝብ አድርሳለች።

2011 . በዜጎች ላይ በደረሰው መፈናቀል አርቲስት ወይኒቱ አንዱር በችግር ላይ መሆኗን ተከትሎ የተለያዩ አካላት ድጋፍ እያደረጉላት ይገኛል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ለአርቲስት ወይኒቱ አንዱር 50 ሺህ ብር እና በግልገል በለስ ከተማ የድርጅት ቦታ ድጋፍ ማድረጉን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አድጎ አምሳያ ተናግረዋል።

 

ግልገል በለስ ከተማ እየተከበረ በሚገኘው የባህል ሳምንት ላይ የተገኘችው አርቲስት ወይኒቱ አንዱር የክልሉ የባህል አምባሳደር ሆና ሆና ተሹማለች።

Read more...

 
ከተለያዩ የመንግስት አካላት ጋር በምን መልኩ መገናኘት ይመርጣሉ?